=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
አንዳንድ ሰዎች በመኝታ ፍራሻቸው ላይ እንደተጋደሙ በነፍሶቻቸው ውስጥ የአለም ጦርነት ያካሂዳሉ። ከዚያም ጦርነቱ ሲያበቃ የጨጓራ በሽታን ፣ የደም ግፊትንና የስኴር በሽታን ማርከው ያርፋሉ። ከክስተቶች ጋር አብረው ይቃጠላሉ፤ በኑሮ ውድነት ይናደዳሉ፤ ዝናብ በመዘግየቱ ይግላሉ፤ የብር ዋጋ በመቀነሱም ይንጫጫሉ። ሁሌም ጭንቀት ውስጥ ናቸው። ትካዜም ያንዣብብባቸዋል።
እኔ ደግሞ የምመክርህ ምድርን በጭንቅላትህ ላይ እንዳትሸከማት ነው። አስከፊ ክስተቶችን እዚያው ምድር ላይ እንደሆኑ ተዋቸው። ጨጓራህ ውስጥ አታስገባቸው። አንዳንድ ሰው ቀልቡ እንደ እስፖንጅ ነው። አሉቧልታዎችንና የመንደር ወሬዎችን ይመጣል። በቀላሉ ይጨነቃል፤ ለሆነ ላልሆነው ይንቀጠቀጣል። ለሁሉም ነገር ውስጡ ይናወጣል። ቀልብ ደግሞ ባለቤቱን የማፍረስና ማንነቱን የመናድ ሃይል አለው።
የሐቅ ጓዶች ግሳፄዎችና ተሞክሮዎች ባላቸው እምነት ላይ ጥንካሬን ይጨምሩላቸዋል። የክህደት ጓዶች ደግሞ ነውጦች ፍራቻቸውን ያባብሱባቸዋል። በአስከፊና በአስቸጋሪ ጊዜያት ደግሞ ከጠንካራ ቀልብ የበለጠ ጠቃሚ ነገር የለም። ምክኒያቱም ጀግና የሆነ ሰው ምንጊዜም ሆደ ሰፊና ፅኑ ነው። በአሏህ ላይ ያለው መተማመን ሥር የሰደደ ነው። መንፈሱ የተረጋጋ ነው። ልበ ሰፊም ነው። ፈሪ ግን በየቀኑ በብዥታ ህልም ፣ ትንቢትና አሉቧልታ ሰይፍ በተደጋጋሚ ራሱን ያደርዳል።
የተረጋጋ ህይወት መኖር ከፈለክ ችግሮችን በድፍረትና በጥንካሬ ተጋፈጣቸው። ቂሎችም እንዳያታልሉህ በሚያሴሩትም አትጠበብ። ከሚያጋጥሙህ ችግሮች በልጠህ ለመገኘት ሞክር። ከጐጂ ነፍሶች በልጠህ ለመበፈርታት ጣር። ከአውሎ ንፋስም የባሰ ጠንክር። እነዚያ ቀልበ ደካሞች አቤት ሲያዝኑ ጊዜ ሲወዘውዛቸው ይኖራሉ። በህይወት ላይ የሚጓጉ ኾነው ታገኛቸዋለህ። ጠንካሮች ግን የአሏህ እገዛ ሁሌም አብሯቸው ነው። ቃሉንም በተስፋ ይጠባበቃሉ። በነሱም ላይ እርጋታን አወረደ።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|